ውድ ኢትዮጵያውያን ወገኖቼ!
የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝን የመከላከል ሥራችን ተጠናክሮ እንዲቀጥል፣ በዓለም የጤና ድርጅት የተጀመረውን የአፍ እና የአፍንጫ መሸፈኛን የሚያስተዋውቅ ዘመቻ ሀገራችን “ማስክ ኢትዮጵያ” በሚል ተቀላቅላለች::
በዚህ የአፍ እና የአፍንጫ መሸፈኛ ዘመቻ የሁላችንም ተሳትፎ ጨምሮ፣ እውቀታችን አድጎ፣ ባህሪአችንም ተለውጦ፣ ወረርሽኙን በተሻለ አቅም መከላከል እንችላለን ብዬ አምናለሁ፡፡
ሁላችንም፣ የአፍ እና አፍንጫ መሸፈኛን በብዛት በማምረት፣ በትክክል በማድረግ፣ እባካችሁ ራሳችንንም፣ ወገኖቻችንንም ከበሽታ እንጠብቅ!
አንድም ሰው በበሽታ እንዲያዝ ፣ የማይተካ ሕይወት እንዲያልፍ ፣ የአገራችን እድገት እንዲስተጏጎል ምክንያት አንሁን!!
የሁላችንም ያልተቋረጠና የተባበረ ጥረት ወረርሽኙን ለማሸነፍ ይሁን!
My fellow Ethiopians,
@WHO has launched the #WearAMask challenge to promote the use of face masks in fighting the spread of #COVID19. Ethiopia has followed suite by launching #MaskEthiopia.
Let us all take part in this campaign by promoting the proper use of face masks as we all work to put a stop to this pandemic.
Wearing masks saves lives!
@drtedros @lia_tadesse