Friday, 20 August 2021 12:06

ፕሬዝደንት ሣህለ ወርቅ ዘዉዴ በኢትዮጵያ የ International Fund for Agricultural Development ተጠሪ የሆኑትን ማዊራ ቺቲማን አነጋግረዋል፡፡ Featured

  • Print
  • Email
ፕሬዝደንት ሣህለ ወርቅ ዘዉዴ በኢትዮጵያ የ International Fund for Agricultural Development ተጠሪ የሆኑትን ማዊራ ቺቲማን አነጋግረዋል፡፡ በዉይይታቸዉ ተጠሪዉ ድርጅቱ በኢትዮጵያ እያካሄደ ስላለዉ ሰፊ የግብርና ዘርፍን ማጠናከርና ማዘመንና ሥራ ገለጻ አድርገዋል፡፡
ድርጅቱ በሀገራችን ከ700 ሚሊዮን ዶላር በላይ በተለያዩ ፕሮጀክቶች ላይ ያወጣ ሲሆን በመቀጠልም ከመንግስት ጋር በቅርበት በመሥራት ሥራዉን ለማስፋፋት ያለዉንም እቅድ ገልጸዋል፡፡ ፕሬዝደንቷ የግብርና ዘርፍ ለሀገራችን ዋነኛ ከሆኑት ዘርፎች አንዱ እንደመሆኑ የተጀመረዉን ሥራ መንግስት ያወጣቸዉን ግቦች በማስፈጸም ድጋፋቸዉን እንዲቀጥሉ አሳስበዋል፡፡

Leave a comment