ኘሬዝዳንት ሣህለወርቅ ዘውዴ የታንዛንያን የውጭ ጉዳይ ሚኒስተር ሊቤራታ ሙላሙላን በጽ/ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል፡፡ ሁለቱ አገሮች የበለጠ ስለሚቀራረቡበት መንገድና ስለ ሴቶች ተሳትፎ ተወያይተዋል፡፡
ታንዛንያ ለመጀመርያ ጊዜ በሴት ኘሬዝዳንት እየተመራች መሆኑና ኘሬዝዳንት ሣህለወርቅ ዘውዴ ከ6 ወራት በፊት በታንዛንያ የሥራ ጉብኝት ማድረጋቸውና የወቅቱ ኘ/ት ማጉፉሊ በድንገት ከማረፋቸው በፊት ያገኟቸው የመጨረሻ ርዕሰ ብሔር መሆናቸው ይታወሳል፡፡