ፕሬዚደንት ሣህለ ወርቅ ዘውዴ ለቶኪዮ ፓራ ኦሎምፒክ ተሳትፎ አስፈላጊውን መመዘኛ ላሟሉ የኢትዮጵያ ቡድን አባላት አሸኛኘት አደረጉ።
የአካል ጉዳተኛ መሆን ማነስ ያለመሆኑን ያነሱት ፕሬዘዳንቷ የሀገራቸው ሰንደቅ አላማ ከፍ ብሎ እንዲውለበለብ ያደርጉ ዘንድ መልካሙን ተመኝተውላቸዋል።
ኢትዮጵያ በፓራ ኦሎምፒክ ውድድር መሳተፍ የሚችሉ በርካታ ዜጎች እንዳሏት የጠቀሱት ተወዳዳሪዎቹ መመዘኛውን ለማሟላት በሚደረገው ጥረት የሚመለከታቸው ሁሉ ድጋፍ እንዲያደርጉ ጠይቀዋል።
ፕሬዝደንቷ የእነርሱ ተሳትፎ ህብረተሰቡና የሚመለከታቸው አካላት አካል ጉዳተኝነት የተሻለ ግንዛቤና ትኩረት እንዲያገኝ በከፍተኛ ደረጃ ይረዳል ብለዋል::
የኢትዮጵያ የፓራ ኦሎምፒክ አባላት በመጪው ቅዳሜ ወደ ቶኪዮ ያመራሉ።