የኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ

 

የኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ

፩. የኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ ከላይ አረንጓዴ፡ ከመሐል ቢጫ ፡ ከታች ቀይ ሆኖ በመሐሉ ብሔራዊ ዓርማ ይኖረዋል። ሦስቱም ቀለማት እኩል ሆነው በአግድም ይቀመጣሉ።
፪. ከሰንደቅ ዓላማው ላይ የሚቀመጠው ብሔራዊ ዓርማ የኢትዮጵያ ብሔሮች፡ ብሔረሰቦች፡ ሕዝቦች እና ሃይማኖቶች በእኩልነትና በአንድነት ለመኖር ያላቸውን ተስፋ የሚያንጸባርቅ ይሆናል።
፫. የፌደራሉ አባሎች የየራሳቸው ሰንደቅ ዓላማና ዓርማ ሊኖራቸው ይችላል። ዝርዝሩን በየራሳቸው ምክር ቤት ይወስናሉ።