የፕሬዚዳንቱ ሥልጣንና ተግባር
፩. የሕዝብ ተወካዮችን ምክር ቤትና የፌዴሬሽን ምክር ቤት ዓመታዊ የጋራ ስብሰባ ይከፍታል።
፪. በዚህ ሕገ መንግሥት መሰረት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ያጸደቃቸውን ሕጎችና ዓለም አቀፍ ስምምነቶች በነጋሪት ጋዜጣ ያውጃል።
፫. ሀገሪቷን በውጭ ሀገሮች የሚወክሉትን አምባሳደሮችና ሌሎች መልዕክተኞች በጠቅላይ ሚኒስትሩ አቅራቢነት ይሾማል።
፬. የውጭ ሀገር አምባሳደሮችንና የልዩ መልዕክተኞችን የሹመት ደብዳቤ ይቀበላል።
፭. በሕግ መሰረት ኒሻኖችና ሽልማቶችን ይሰጣል።
፮. በጠቅላይ ሚኒስትሩ አቅራቢነት በሕግ በተወሰነው መሰረት ከፍተኛ የውትድርና ምዕረጎችን ይሰጣል።
፯. በሕግ መሰረት ይቅርታ ያደርጋል።